አላማ
ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘመናዊ መዋቅር ያላት ሆና እንድትተዳደር በተደነገገው ህግ ቃለ ዓዋዲ መመስረት ጋር አብሮ የተጀመረ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው። ሰበካ ጉባኤ በቃለ አዋዲ አንቀፅ 5 መሰረት የሚከተሉት አለማዎች አሉት:
- ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ
- የቤተክርስቲያንን አገልጋዮች ሐዋርያዊ ተግባር ለማደራጀትና እንደዚሁም ችሎታቸውንና ኑሮአቸውን ለማሻሻል
- ምዕመናንን ለማብዛት እንደዚሁም በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ
- የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ለማሻሻልና በማናቸውም ጉዳይ ራሷን ለማስቻል ነው
አባላት
❖ መልአከ ሰላም ቀሲስ ሚስጢሩ
አስተዳዳሪ እና የሰበካ ጉባኤው ሊቀመንበር
❖ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ጥላሁን አበበ
ዋና ጸሐፊ
❖ መጋቢ ሥረአት ቀሲስ አንተነህ ወርቅነህ
ቄሰ ገበዝ
❖ አቶ መኮንን ደጄኔ ብዙነህ
ምክትል ሊቀመንበር
❖ ወ/ሮ ገነት ደስታ ቱሉ
ሂሳብ ሹም
❖ ወ/ሮ ሃይማኖት ሞላ ጤናው
ገንዘብ ያዥ
❖ ወ/ሮ ሃና ገብረስላሴ
ምክትል ጸሐፊ
❖ ወ/ሮ የሺ ተክሉ
ረዳት ገንዘብ ያዥ
❖ ወ/ሮ ታሪክ ገዳሙ
ህዝብ ግንኙነት
❖ አቶ ደስታ ውድነህ
ቴክኖሎጂ አማካሪ