የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መሠረተ ሃይማኖት በዝርዝር ከመግለፃችን አስቀድሞ ክርስትና በኢትዮጵያ እንዴትና መቼ ተጀመረ የሚለዉን ነጥብ በአጭሩ እንመለከታለን ሀገራችን ኢትዮጵያ ክርስትናን በዘመነ ሐዋሪያት በቀዳሚነት ከተቀበሉ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑ ሀገሮች አንዷ ናት። ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ ቀደም ብሎ ኢትዮጵያዉያን የአይሁድ ሃይማኖት ተቀብለዉ ለብዙ ዘመን እንደቆዩ የታሪክ ጥናት ባለሙያዎች ይናገራሉ።
እንደ ታሪክ ፀሃፊዎች ምስክርነት በኢትዮጵያ በአንድ አምላክ ማመን (Monotheism) ኃላም የአይሁድ ሃይማኖት (Judaism) ለብዙ ዘመናት ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነዉ እንደቆዩ ይናገራሉ።
በተጨማሪም የንግስተ ሳባም የእየሩሳሌም ጉዞና “አንተን የወደደ በእስራኤልም ዙፋን ያስቀመጠህ እግዝአብሔር የተባረከ ይሁን ” 1ኛ ነገ 109 በማለት ለንጉሱ ሰሎሞን መናገሯ ማድነቋ ኢትዮጵያዉያን አስቀድመዉ በአንድ አምላክ ያምኑ እንደነበር ሌላዉ ማሳያ ነዉ የታቦት ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት በእየሩሳሌም የዴር ስልጣን ገዳማት ለ ኢ/ያ መሠጠት ዛሬም ድረስ በኩራት ለዓለም የምናወራዉ የታሪክ እዉነት ማረጋገጫና በሀገራችን ከ2000 ዓመታት አስቀድሞ መስዋዕተ ኦሪት ይሠዋ እንደነበር ያሳያል።
ኢትዮጵያዉያን የአይሁድን ሃይማኖት ከተቀበሉ በኃላ በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሳለሙ ይሄዱ ነበር ት.ሶ 3፡10 ይኸዉ ጉዞ እስከ ክርስትናዉ መምጣት የቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግስት ህንደኬ ጃንደረባ (የገንዘብ ሚንስትር) የሆነዉ ባኮስ በ 34 ዓ.ም (ከክ ልደት በኃላ) ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ ሲመለስ በሠረገላዉ ተቀምጦ የኢሳያስን የትንቢት መጽሐፍ ያነብ እንደነበር እና የመጽሐፍንም ምስጢር ፊሊጶስ በተረጎመለት ጊዜ “ በዉሃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድር ነዉ ብሎ በመጠየቅ እየሱስ ክርስቶስ ህያዉ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በማመን እንደተጠመቀ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል የሐዋ 8፡26 አዉሳብዮ የተባለዉ ታዋቂ የ ቤ/ክን ታሪክ ፀሐፊ “Historical Ecclesia` በተሰኘዉ መፅሐፉ ከዕብራዉያን ወገን ያልሆነ የመጀመሪያዉ የክርስትና እምነት ፊሬ ብሎ ሲገልፀዉ ሄሮኒሞክስ ደግሞኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ ወደ ሃገሩ ተመልሶ ማስተማሩን ይተርካል። በ4ተኛ መቶ ክፍለ ዘመንም ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ ሁሉ፤ በአዋጅ ተቀብሎታል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን መሠረተ እምነት ዳግማ በመባል ይታወቃል። ዳግማ ማለት ቃሉ የግሪክ (የጽርዕ) ሲሆን ትርጉሙም የማይሻር የማይለወጥ የማይቀየር የማያልፍ ማለት ነዉ ይህም ማለት ዓለማትን በፈጠረ ፍጥረቱንም በሚመግብ ሁሉን አሳልፎ ለዘላለም የሚኖር እግዚአብሔርን ማመን ማለት ነዉ።