6:30am - 10:00am
"እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር፥ ከፍሬህም ሁሉ በኵራት" - መጽሐፈ ምሳሌ 3:9
እታች ያለውን ሊንክ ነክተው ቅጹን ያውርዱ
በአሁኑ ወቅት 311 አባላት አሉን።
ኢትዮጵያዉያን የአይሁድን ሃይማኖት ከተቀበሉ በኃላ በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሳለሙ ይሄዱ ነበር ት.ሶ 3፤10 ይኸዉ ጉዞ እስከ ክርስትናዉ መምጣት የቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግስት ህንደኬ ጃንደረባ (የገንዘብ ሚንስትር) የሆነዉ ባኮስ በ 34 ዓ.ም (ከክ ልደት በኃላ) ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ ሲመለስ በሠረገላዉ ተቀምጦ የኢሳያስን የትንቢት መጽሐፍ ያነብ እንደነበር እና የመጽሐፍንም ምስጢር ፊሊጶስ በተረጎመለት ጊዜ “ በዉሃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድን ነዉ ብሎ በመጠየቅ እየሱስ ክርስቶስ...
የደብረ መድኃኒት ኢየሱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በውድብሪጅ ቨርጅንያ የሚጊኝ ሲሆን በአካባቢው በሚገኙ በጎ ምዕመናን ተነሳሽነት አሳቡ ከተጀመረ በኋላ በአንድ ላይ በመሰባሰብ በማኅበርና በጸሎት እንዲሁም ወንጌልን በመማር ሲደራጅ ቆይቶ በ2610 Omisol Rd Woodbridge, VA 22192 አድራሻ በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ግንቦት 15/2002 (May 23, 2010) በዕለተ ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት በወረደበት ቀን) ቅዳሴ ቤቱ ሊጀመር ችሏል። ....
ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘመናዊ መዋቅር ያላት ሆና እንድትተዳደር በተደነገገው ህግ ቃለ ዓዋዲ መመስረት ጋር አብሮ የተጀመረ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው። ሰበካ ጉባኤ በቃለ አዋዲ አንቀፅ 5 መሰረት የሚከተሉት አለማዎች አሉት። ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ፤ የቤተክርስቲያንን አገልጋዮች ሐዋርያዊ ተግባር ለማደራጀትና እንደዚሁም ችሎታቸውንና ኑሮአቸውን ለማሻሻል፤ ምዕመናንን ለማብዛት እንደዚሁም በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ...
"ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።" - የዮሐንስ ወንጌል 6፡53
"እንዲህም አላቸው። 'ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።' - የማርቆስ ወንጌል 16፡15
"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" - የማቴዎስ ወንጌል 19፡6
"ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" - የዮሐንስ ወንጌል 3፡5
"እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።" - የማቴዎስ ወንጌል 18፡18
"ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።" - መጽሐፈ ምሳሌ 22፡6